ለኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል ።
የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በተሸጋገረበት ወቅት የህዝቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን የአማራ ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ላቀ ጥላዬ ለኢዜአ እንደገለጹት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማጠናቀቅ የአገራችን ሉአላዊነትና የፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ጉዳይ ነው።
መንግስትና ህዝብ በራሳቸው ገንዘብ፣ ጉልበትና እውቀት የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅሌት ከቀን በመስራታቸው ግድቡ ውሃ መሙላት በሚጀምርተት ደረጃ ማድረስ እንደተቻለ ገልፀዋል ።የአማራ ክልል ህዝብም በቦንድ ግዥና ሌሎች የሃብት ማሰባሰቢያ መንገዶች እስከ አሁን ከ1ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ በመሰብሰብ ለግድቡ ግንባታ ጥቅም ላይ እንዲውል አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ከዚህ ውስጥ 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚሆነው ገንዘብ የተሰበሰበው የኮሮና ቫይረስ በተከሰተበት በዚህ ዓመት መሆኑ ህዝቡ የግድቡን ግንባታ የህልውና ማረጋገጫ ጉዳይ አድርጎ ለመውሰዱ ማሳያ ነው ብለዋል።በቦንድ ግዥም የክልሉ ባለሃበት፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የመንግስት ሰራተኛውና ሌላውማህበረሰብ የነቃ ተሳትፎ ማድረጉን ሃላፊው አስታውቀዋል።
ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጋር ተያይዞ ከመጣው የኢኮኖሚ መዳከም አንጻር መንግስት በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ ገንዘብ ለመሰብሰብ ባይችልም ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት ያደረገውድጋፍ ግን የሚበረታታ ነው ብለዋል ።
በተጨማሪም ግድቡ በደለል እንዳይሞላና ረጅም አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል በአፈርና ውሃ እቀባ ስራ 24 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ግምት ያለው የጉልበትና የእውቀት አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።