EthiopiaPolitics

ባለፈው ሰኔ በአሶሳ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

ያን ግዜ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ለድጋፍ አጽድቋል፡፡

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግስት በግጭቱ ምክንያት ህይወታቸው ላለፈ 16 ግለሰቦች ቤተሰብ ለእያንዳንዳቸው 30 ሺ ብር፣ በግጭቱ ምክንያት ከባድ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው 11 ግለሰቦች ለእያንዳንዳቸው 20ሺ ብር እንዲሁም በግጭቱ ምክንያት ቀላል ጉዳት ለደረሰባቸው 78 ግለሰቦች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 10 ሺ ብር ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ክልሉ ንብረታቸው ለወደመባቸው ከ1ሺህ -5ሺ ብር ግምት ላለው ንብረት የቀረበው መጠን እንዲከፈል የወሰነ ሲሆን፣ ከብር 5001 ጀምሮ ያለውን ግምት በተመለከተ በ70% ተሰልቶ በድምሩ 589,665.40 ብር እንዲከፈላቸው መወሰኑንም  ከኢቢሲ ያገኘዉን መረጃ ያመለክታል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami