የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳች ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ካሣሁ ጎርፌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ
በዝግጅቱ አድስቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚያስችለንን ቃል የምንገባበት ከመሆኑም በላይ በሁለም የህብረተሰብ ከፍል እና በመላው ሀገሪቱ የመነቃቃት ስሜት በሚፈጠርበት በመደመር ስሜት በውጭ ሀገር የሚኖሩትን ጨምሮ አዲሲቷ ኢትዮጵያ በጋራ የምንገነባበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በዝግጅቱ ከ 2 መቶ በላይ ኤርትራውያን ለመጋበዝ ከውጭ ጉዳይ ጋር በጋራ በመሆን እየሰሩ እንደሆነ አቶ ካሳሁን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በውጭ ሀገራት የቆዩ የኪነጥበብ በለሞያዎች ታመኝ በየነ እና አለምፀሃይ ወዳጆ ከሠሞኑ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመጡ ሚኒሰትር ድኤታው ገልጸዋል፡፡