EthiopiaPolitics

የሶማሌ ክልልን ከኢትዮጵያ መገንጠል የማይታሰብ ነው አሉ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፋ ዑመር

የሶማሌ ክልልን ከኢትዮጵያ መገንጠል የማይታሰብ ነው አሉ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፋ ዑመር

አርትስ 19/02/2011

 የሶማሌ ህዝብ ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር በሰላም ለመኖር የሚፈልግ ህዝብ መሆኑን ያረጋገጡት የክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፋ ዑመር ይህንን ህዝብና እና ክልሉንከኢትዮጵያ መገንጠል የማይታሰብ ጉዳይ ነው ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በግል ማህበራዊ ድረገጻቸው እንዳስገነዘቡት በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ጋር በአስመራ በተፈፀመ ስምምነት የሶማሌህዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብቱን ተጠቅሞ  ህዝበ ውሳኔ እንዲያደርግ ከስምምነት ላይ ተደርሷል በሚል የቀረበው ዘገባ ሃሰተኛ ነው ብለዋል።በስምምነቱ ወቅትስለ ህዝበ ውሳኔም ሆነ ስለ መገንጠል ጉዳይ ለውይይት አልቀረበም፤ ስምምነትም አልተፈረመበትም ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፡፡
አስመራ ላይ በተደረገው ስምምነት ኦብነግ የትጥቅ ትግሉን አቁሞ በሰላማዊ መንገድ፣ በሃገር ውስጥ ገብቶ እንዲንቀሳቀስ ነው የተስማማው ያሉት የክልሉ ፕሬዚዳንት ፤የህዝበውሳኔና የመገንጠል ጉዳይ ፈፅሞ አልተነሳም ብለዋል።

በምስራቅ ኢትዮጵያ በኩል ያለው ሉአላዊነት የሚጠበቀው በሶማሌ ህዝብ ፍቃድና ፍላጎት ብቻ መሆኑንም ተናግረዋል።

አስመራ ላይ ከኦብነግ ጋር የተደረሰው የሰላም ስምምነት የክልሉን ሰላም ለማይሹ ኃይሎች ደስታ አልፈጠረም ያሉት አቶ ሙስጠፋ በዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተጀመረውንለውጥ ለማደናቀፍና ለማኮላሸት የሚደረግ ማናቸውም ጥረት ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

በግጭትና በአለመረጋጋት በሚታወቀው የሶማሌ ክልል በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የሚደረግበትን ምዕራፍ ጀምረናል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ።

ሁሉን በእኩል አካታችና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠር ጠንክረን እንታገላለን” ብለዋል-በማህበራዊ ድረ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami