ዋሽንግተን በቴህራን ላይ ከመቼውም ጊዜ የከፋ ያለቸውን ማዕቀብ ጣለች
አርትስ 26/02/2011
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በኢራን ለይ የጣለው አዲሱ ማዕቀብ በተለይ የነዳጅ ምርቷን በእጂጉ እንደሚጎዳው የዓለም መገናኛ ብዙሀን በፊት ገፆቻቸው አስነብበዋል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው የአሁኑ ማዕቀብ ከ700 በላይ የሚሆኑ ተቋማት፣ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ ታላላቅ ባንኮች፣ ነዳጅ ላኪ ኩባንያወች እዲሁም የአየር እና የየብስ መጓጓዣወችን ዒላማ ያደረገ ነው፡፡
የአሜሪካ ድርጊት ያስቆጣቸው ኢራናዊያን ሞት ለአሜሪካ የሚል መፎክር አንግበው በአደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ታይተዋል፡፡
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በሰጡት መግለጫ ኢራን በየመን ለተፈጠረው ቀውስና በህፃናት ላይ እየተፈጸመ ላለው ጥቃት ዋነኛ ተጠያቂ ናት ብለዋል፡፡
የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሮሀኒ በበኩላቸው የአሜሪካ ማዕቀብ ሀገራቸው ነደጅ ወደ ፈለገችበት ሀገር ለመላክ እንደማያግዳት በእርግጠኝነት እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ አሁን በኢራን ላይ የተጣለው ማዕቀብ ከአሁን ቀደም ከጣልናቸው ማዕቀቦች ሁሉ የከፋ ነው ኢራን ምን ልታደርግ እንደምትችል እናያለን በማለት ተናግረዋል፡፡