በካሜሮን በታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱ 79 ተማሪዎች ተለቀቁ
አርትስ 29/02/2011
በካሜሮን ሰሜናዊ ምስራቅ ግዛት ከሚገኝ አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ በታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱ 79 ተማሪዎች መለቀቃቸው ተነገረ፡፡
እስካሁን የትምህርት ቤቱን ርዕሰ መምህር ጨምሮ አንድ መምህርና ሾፌር አሁንም በእገታ ላይ ናቸው፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው የሀገሪቱ መንግስት ታጋቾችን ለማስለቀቅ በትናንትናው ዕለት በሄሊኮፕተር የታገዘ ፍለጋ ማድረግ ጀምሮ ነበር።
ነገር ግን የተለቀቁት 79 ተሪዎች በምን ሁኔታ ሊለቀቁ እንደበቁ የታወቀነገር የለም።