አዲስ አበባ ለአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ ጉባዔ ዝግጅቷን አጠናቃለች
አርትስ 29/02/2011
ከህዳር 8-9 አዲስ አበባ ውስጥ ለሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ ጉባዔ አስፈላጊው ቅድመዝግጅት መጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በጉባዔው የ45 ሃገራት መሪዎችና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም እንዳሉት ጉባኤው በህብረቱ ማሻሻያ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኙ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ጉባዔተኞችን ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ቃል አቀባዩ በሳምንታዊ የፕሬስ መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለጉባዔው ስኬት የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።