SportSports

በእግር ኳስ ጨዋታ አጋማሽ የእናታቸው ሞት የተነገራቸው ዳኛ ግጥሚያውን በብቃት መርተዋል

በእግር ኳስ ጨዋታ አጋማሽ የእናታቸው ሞት የተነገራቸው ዳኛ ግጥሚያውን በብቃት መርተዋል

አርትስ ስፖርት 12/03/2011

በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለመግባት ኔዘርላንድስ በቬልቲንስ አሬና ጀርመንን ታስተናግዳለች፤ ይህን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የመሩት ደግሞ ሮማኒያዊው አልቢትር ኦቪዲዩ ሃቴንጋ ናቸው፡፡

አልቢትር ሃቴንጋም ጨዋታውን በብቃት መምራት ችለዋል፡፡

ጀርመን በ ቲሞ ዌርነር እና ሊሮይ ሳኔ ጎሎች ጀርመን 2 ለ 0 ስትመራ ቆይታ ኔዘርላንድስ በፕሮሜስ ግብ ወደ ጨዋታ በመመለስ ሙሉ ግጥሚያው ሊጠናቀቅ ጭማሪ ደቂቃ ላይ በነበረበት ጊዜ አምበሉ ቨርጅል ቫን ዳይክ ግብ በማስቆጠር ሀጉሩን ነጥብ እንድታገኝና ወደ ግማሽ ፍፃሜው እንድትቀላቀል አግዟል፤ ከደቂቃዎች በኋላ ጨዋታው መጠናቀቁን ዳኛ ኢቪዲዬ ሃቴጋን ስሜታዊ ሆነው በፊሽካቸው ያበስራሉ፤ በዚህ ጊዜ አጠገባቸው የነበረው ቫን ዳይክ ሰሜታዊነታቸውን አስተውሎ ይጠይቃቸዋል፤ በጨዋታው የዕረፍት ጊዜ ወላጅ እናታቸውን በሞት መነጠቃቸው አንደተረዱ ይነግሩታል፤ ያኔ ቫን  የሃቴንጋን አናት በመያዝ አንገቱ ስር በመወሸቅ ያፅናናቸዋል፡፡

ቫን ዳይክ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ ለ Voetbal International በሰጠው አስተያየት ‹‹ሰውየው አዝኗል፤ አይኖቹ ላይ የእንባ ዘለላ አስተዋልኩ ምክንያቱ ደግሞ እናቱን በሞት አጥቷቸው ነው›› ብሏል፡፡ ‹‹ጨዋታውን በስርዓት መርቷል፣ እንዲበረታም ምኞቴ ነው፤ ትንሽ ነገር ነው ያደረኩት ነገር ግን ይረደዋል የሚል ተስፋ አለኝ›› ሲል ጨምሯል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami