ቡናን የኢትዮጵያ ገፅታ መገለጫ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ
አርትስ 27/03/2011
በመስቀል አደባባይ ‹‹ኑ ቡናን ለሰላም እንጠጣ›› በሚል መሪ ሀሳብ ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተወጣጡ ሰዎች በተገኙበት ቡና የማፍላት ስነስረአት ተካሂዶ ውሏል፡፡
ዝግጅቱ መጪውን 13ኛ የብሔር ብሄረሰቦች በአል መዳረሻ ሲሆን በአሉ በዚህ አመት ከሚከበርባቸው መንገዶች አንዱ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚያጠናክር መሆኑን ሰምተናል፡፡
የአዲስ አበባ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ረ/ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ቡና ከኢትዮጵያዊን ጋር ትልቅ ትስስር እንዳለው ይናገራሉ፡፡
ይህንን ስርዓት የኢትዮጵያ ገፅታ መገለጫ ለማድረግ ፣ ለማስተዋወቅ እና በአለም ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑንም ሃላፊው ነግረውናል፡፡
እንደየ ብሄረሰቡ ይለያይ እንጂ የቡና አፈላል ስነ-ስረአቱ፣ ጉርብትናን ማጠናከሩ ፣ ትስስርን መፍጠሩ እና መመራረቁ በሁሉም ኢትዮጲያዊያን ዘንድ የሚፈጸምና ተቀባይነት ያለዉ ነው፡፡