አርትስ ስፖርት 02/04/2011
የዘንድሮውን የባላንዶር ክብር ሉካ ሞደሪች ከማሸነፉ ውጭ፤ ሊዮኔል ሜሲና ክርስቲያኖ ሮናልዶ የባለፉት 10 ዓመት የባላንዶር ክብርን እኩል ተካፍለዋል፡፡
የ33 ዓመቱ ፖርቱጋላዊ ማድሪድን ለቆ ከባለፈው ክረምት ጀምሮ በአሮጊቷ ዩቬንቱስ እያሳለፈ ይገኛል፤ የጣሊያን ቆይታ ጅማሮው አመርቂ ባይሆንም ቀስ በቀስእየተላመደ ነው፡፡
ሮናልዶ ከ ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት ጋር ባደረገው ቆይታ ሜሲ ናፍቆት ይሆን እንደሁ ተጠይቆ እንዳልናፈቀውና ምናልባት ሜሲ እርሱን ሊናፍቅ እንደሚችል ተናግሯል፡፡
እርሱ ገራሚ ተጫዋች ነው፣ ጥሩ ሰው ነው፤ ነገር ግን እዚህ ሁኘ ምንም ነገር አይናፍቀኝም፡፡ ይሄ አዲሱ ህይወቴ ነው፣ ለዚህም ደስተኛ ነኝ ሲል ተናግሯል፡፡
ሮናዶ አክሎ እኔ በእንግሊዝ፣ ስፔን፣ ጣሊያን፣ ፖርቱጋልና በብሔራዊ ቡድን ተጫውቻለሁ፤ አርሱ ግን አሁንም ስፔን ነው፤ ምናልባት እርሱ እኔን በጣም ይፈልገኛል፤ለእኔ ህይወት ፈተና ነች፣ መፈተንም እወዳለሁ፣ ሰዎችን ማስደሰት እወዳለሁ ብሏል፡፡
አንድ ቀን ወደ ጣሊያን እንዲመጣ እፈልጋለሁ፤ ያለው ፖርቱጋላዊው ሜሲ እንደ እኔ ፈተናን መቀበል ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን አሁንም እዛው መሆን የሚያስደስተውከሆነ ውሳኔውን እንደሚያከብር ገልጧል፡፡