EducationEthiopia

በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት መፍጠር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ውይይት ተካሂዷል

በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት መፍጠር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ውይይት ተካሂዷል

አርትስ 03/04/11

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደውን ይህንን ውይይት ያዘጋጀው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሲሆን በውይይቱም በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ የሚነሱ ግለሰባዊ ግጭቶች የብሄር መልክ እየያዙ የመማር ማስተማር ሂደቱን እያስተጓጎሉ ነው ተብሏል።

በአዲስ አበባ የዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የቦርድ ሰብሳቢዎች እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት በተካሄደውና በዩኒቨርሲቲዎች በሚስተዋሉ ግጭቶች ዙሪያ ባተኮረው በዚሁ ውይይት “በዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዴት መፍጠር ይቻላል?” የሚል ጥናታዊ ሪፖርት ቀርቧል፡፡

በዩኒቨርሲቲዎች የተሟላ የአመራር ምደባ አለማድረግና በምክትል ወይም በተወካይ ፕሬዝዳንት የሚመሩ ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር መብዛቱ ስራውን በተሟላ መልኩ ለማካሄድ አስቸጋሪ አድርጎታል ነው የተባለው፡፡

የቦርድ አመራር አባላትን የሙያ ስብጥር አለመጠበቅ፣ በቅንጅት የመምራት ችግር፣ የዩኒቨርሲቲ አመራር አካላት በየዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ተቀባይነት ማጣት እና የመምህራንና የመሰረተ ልማት አለመሟላት በችግርነት ተጠቅሰዋል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami