አዲስ አበባ በኳታር ፋውንዴሽን የኩላሊት ህክምና ማዕከል ይገነባላታል ተባለ
አርትስ 04/04/2011
የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን የኳታር ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ ከተማ የኩላሊት ህክምና አገልግሎትን ብቻ የሚሰጥ ማዕከል ለመገንባት በኢትዮጵያ ከኳታር አምባሳደር ሀማድ አል – ዶሳሪ ጋር ተስማምተናል ሲሉ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል።
ዶክተር አሚር አማን ስምምነት ላይ የደረሱት ከአምባሳደር ሀማድ አል-ዶሳሪ ጋር ከተወያዩ በኋላ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ ትናንት ሁሉን ዓቀፍ የጤና ተደራሽነት ቀን መሆኑን አስታውሰው፥ የሰው ልጅ ያለምንም ልዩነትና የፋይናንስ ችግር የሚያስፈልገውን መሰረታዊ ጤና አገልግሎት የማግኘት መብት እንዳለው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡