አርትስ ስፖርት 12/04/2011
ግሪክ ቀዳሚ ሊጓ የግሪክ ሱፐር ሊግ ይሰኛል፤ ይህ ሊግ በደጋፊዎች፣ ተጫዋቾችና ክለቦች ብጥብጥ በተደጋጋሚ ይታመሳል፡፡ አሁን ደግሞሁሉንም የሊግ ጨዋታዎች እንዲካሄዱ የማያስደርግ ክስተት ሊጉን ገጥሞታል፡፡
የፊፋ የዳኝነት ፍቃድ ያላቸው አርቢትር ታናሲስ ዚሎስ ከመኖሪያ ቤታቸው ውጭ ጥቃት ይሰነዘርባቸዋል፤ ከዚያም ወደ ሆስፒታል አቅንተውሀሙስ ጭንቅላታቸው እና እግራቸው ላይ ህክምና ከተደረገላቸው በኋላ ከሆስፒታል ወጥተዋል፡፡
የዳኞች ማህበር እንዳለው ‹‹በዚህ አሳዛኝ ድርጊት ላይ ዝርዝር መረጃ አስክናገኝ ወደ ስራ ገበታችን አንመለስም›› ብለዋል፡፡ የሊጉ አስተዳዳሪምየዚህ ሳምንት የጨዋታ መርሃግብሮች እንደማይከናወኑ አስታውቋል፤ ላልተወሰነ ጊዜም ተራዝመዋል፡፡
ባለፈው የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዳኞች ላይ ጥቃት መድረሳቸው ከአንድም ሁለቴ በተለያዩ ስታዲየሞች መመልከታችንይታወሳል፡፡
‹‹በባልደረባችን ታናሲስ ዚሎስ እና ዳኞች ላይ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ባለው የፈሪነት ጥቃት የተሰማንን ብስጭት ለመግለፅ እንገደዳለን፤እነዚህ ሰዎች ሁሌ እኛን እያሸበሩ እንዲቀጥሉ አንፈቅድም›› ሲል ባወጣው መግለጫ ጨምሮ ገልጧል፡፡
አርቢትር ዚሎስ በዚህ ወር መጀመሪያ በሊጉ ኦለምፒያኮስ ከ ዣንቲ 1 ለ 1 አቻ የተለያዩበትን ጨዋታ መምራታቸው የታወሳል፡፡
የኦለምፒያኮስና ፓናቲኒያኮስ ክለቦች በተወካዮቻቸው በኩል የተፈፀመውን ድርጊት አውግዘዋል፡፡ ሱፐር ሊጉ በስርዓት አልበኝነት ምክንያትበተደጋጋሚ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ የሊግ መርሃግብሮች የሚቆራረጡ ሲሆን የግሪክ ባለስልጣናት ታላላቅ የደርቢ ፍልሚያዎችን ከውጭበሚመጡ ዳኞቾ ለማስመራት መወሰናቸው ይታወቃል፡፡