AfricaEthiopia

ድህነትን ለማጥፋት ዓለም ከቻይና መማር አለበት ተባለ

አርትስ ታህሳስ 12 2011

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዓለማችን በገጠር የተስፋፋውን ድህነት ለመቀነስ ብሎም ለማፋጥት ያስችለኛል ያለውን ድንጋጌ አፅድቋል፡፡

ይህ ድንጋጌ በድርጅቱ ሲፀድቅ የመጀመሪያው ሲሆን ትኩረቱን ያደረገውም በታዳጊ ሀገራ በገጠር ያለውን አስከፊ ድህነት ለማጥፋት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶን ማስፋፋት ላይ ነው፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው በርካታ የድርጅቱ አባል ሀገራት ቻይና የተከተችውን የእድገት ጎዳና ቢከተሉ ውጤታማ እንደሚሆኑ አምነውበታል፡፡

ድርጅቱ ይህን አዲስ ስትራቴጂ የቀየሰው በታዳጊ ሀገራት ያለውን ድህነት በማጣፋት የ2030 ድህነትን ከዓለማችን ላይ የማጥፋት አጀንዳን ለማሳካትም በማለም ነው፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቻይናው ተወካይ ማ ዛወሹ ሀገራቸው የተከተለችውን መንገድ ሀገራት በዚህ መልኩ እውቅና መስጠታቸውና ይህን ስምምነት ማድረጋቸው  ትልቅ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡

አዲስ የተደረገው ስምምነት በሚቀጥለው ዓመት በሚካሄደው የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ ለዋና ፀሀፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የቤት ስራ ተሰጥቷቸዋል ነው የተባለው፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami