ናይጀሪያ የቦኩ ሃራም ታጠቂ ቡድን 14 የፀጥታ ሀይሎቼን ገድሎብኛል አለች
አርትስ 17/04/11
የሀገሪቱ መከላከያ ተቋም 14 የፖሊስ እና የጦር ሰራዊት አባላት በታጣቂው ቡድን ድንገተኛ ጥቃት መገደላቸውን አስታውቋል፡፡
አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ወታደሮቹ በታጣቂው ቡድን የተገደሉት በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ዮቤ ግዛት በፀጥታ ማስከበር ስራ ላይ በነበሩበት ወቅት ነው፡፡
የናይጀሪያ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ኦኒያማ ንዋቹኩ ጥቃት አድራሾቹን ተከታትሎ የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ የተመደበ ወታደራዊ ሀይል ታጣቂዎቹ ይገኙበታል ወደተባለው ስፍራ ተሰማርቷል ብለዋል፡፡
የናይጀሪያ ጦር ሰራዊት የቦኩ ሀራምን የሚሊሻ ቡድን ለማጣፋት ለዓመታት ከባድ ውጊያ ቢያደርግም እስካሁን ግን የሚፈልገውን ድል ማስመዝገብ አልተቻለውም፡፡
ፕሬዝዳንት ሞሀማዱ ቡሀሪ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ለህዝባቸው የገቡት ቃል ይህን ቡድን ማጥፋትና በቡድኑ ነጋ ጠባ የሚታደኑት ልጃገረዶች እንደልባቸው እንዲማሩ ማድረግ ነበር፡፡
ይሁን እና ቡድኑ ከመዳከም ይልቅ ድሮንን ጨም ዘመናዊ ጦር መሳሪያዎችን በመጠቀም በወታደራዊ እና ሲቪል ተቋማት ላይ ጥቃቱን ማጠናከሩ ለቡሀሪ ትልቅ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል፡፡