ኤርትራ ከኢትዮጵያ ለቀረበላት የእርቅ ጥያቄ የሰጠቸው አወንታዊ ምላሽ ለሰላም ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ነው የተባለው፡፡
ታዲያ ለዚህ የሰላም አጋዥነቷ የተጣለባት ማእቀብ እንዲነሳላት ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታ ድርጅት ጥያቄ አቅርባ ነበር፡፡ ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው አሁን ላይ ድርጅቱ የኤርትራ ማእቀብ ይነሳ ወይም አይነሳ በሚለው ሀሳብ ዙሪያ ምክክር አድርጓል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስዊድን አምባሳደር ኦልፍ ስኩግ እንዳሉት ኤርትራና ሶማሊያ ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት በጋራ እንሰራለን ማለታቸውም የጸጥታው ምክር ቤት በአድናቆት ይመለከተዋል፡፡
አምባሳደሩ አሁን በምስራቅ አፍሪካ ታሪክ ሲሰራ እየተመለከትን ነው ድርጅቱም ይህን መልካም ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በኤርትራና በጂቡቲ መካከል ያለው የድንበር ውዝግብ በአፋጣኝ መፍትሄ አግኝቶ ሀገሮቹ ወደ ቀደመ ወዳጅነታቸው እንዲመለሱ ጥሪ ማቅረቧንም አምባሳደሩ እድንቀዋል፡፡