Africa

የሱዳን ባለስልጣናት ተቃዋሚዎችን አርፋችሁ ተቀመጡ እያሉ ነው

የሱዳን ባለስልጣናት ተቃዋሚዎችን አርፋችሁ ተቀመጡ እያሉ ነው

የሱዳን ባለስልጣናት በፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ላይ የመፈንቅለ መንግስት ጥሪ አድርገዋል ለተባሉ ተቋዋሚ ፓርቲዎች ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡

በተቃውሞ ሰልፍ መንበራቸው የተነቃነቀው አልበሽር በሀገሪቱ የተከሰተውን አለመረጋጋት ለማብረድ ኢኮኖሚያዊ መሳያዎችን ለማድረግ ቃል ቢገቡም ሰሚ ያገኙ አይመስልም፡፡

በመላ ሀገሪቱ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ያሉት ዜጎች ፕረዝዳንቱ ስልጣናቸዉን በአስቸኳይ እንዲለቁ ተደጋጋሚ ጥረት ከማቅረብ አልተቆጠቡም፡፡

አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው ሱዳንን እየመራ ያለው ናሽናል ኮንግረስ ገዥው ፓርቲ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰውን የናሽናል ፍሮንት ፎር ቼንጅ የተባለውን ፓርቲ በፕረዝዳንቱ ላይ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ አሲረዋል በማለት  ከሷል፡፡

የገዥው ፓርቲ ፀሀፊ አብደል ራህማን አል ከዲር ይህ ጥርጣሬ እውነት ሆኖ ቢገኝ በዚህ ተግባር የተሰማሩ ሁሉ  የሀገሪቱን ህገ መንግስት እንዳፈረሱ ይወቁ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

የ22 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው ናሽናል ፍሮንት ፎር ቸንጅ እና በቀድሞው የሱዳን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሙባረክ አል ፋዲል የሚመራው ኡማ ፓርቲ በጋራ ባደረጉት ስብሰባ የሽግግር ምክር ቤት እንዲቋቋም ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

በሱዳን በተከሰተው የዋጋ ንረት ላለፉት ሁለት ሳምንታት ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ በወጡ ሰዎችና በፖሊሶች መካከል ግጭት ተፈጥሮ በትንሹ 19 ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡

 

 

 

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami