Uncategorized

የቀድሞው የእስራኤል ሚኒስትር ለጠላት በመሰለል የእስር ቅጣት ይጠብቃቸዋል

የቀድሞው የእስራኤል ሚኒስትር ለጠላት በመሰለል የእስር ቅጣት ይጠብቃቸዋል

ቀደም ባለው ጊዜ የኢነርጂ ሚኒስትር በመሆን ሀገራቸው እስራኤልን ያገለገሉት ጎኔን ሴጌቭ የሀገርን ሚስጥር ለጠላት አሳልፈው ሰጥተዋል ተብለው ነው ክስ የተመሰረተባቸው፡፡

ሴጌቭ ጥፈተኛ በተባሉበት የሀገር ክህደት ወንጀል በቀላሉ የ11 ዓመት የእስር ቅጣት  እንደሚጠብቃቸው የእስራኤል የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የእስራኤሉ ሀራትዝ እንደዘገበው የቀድሞው የፓርላማ አባል እና የኢነርጂ እና የመሰረተ ልማት ሚኒስትር የሀገሩን ሚስጥር አሳልፈው የሰጡት የእስራኤል  ቀንደኛ ጠላት ለሆነቸው ኢራን መሆኑ ትልቅ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

ተከሳሹ ግን በምርመራ ወቅት እኔ ኢራናዊያንን በማታለል በሀገሬ ዘነድ ጀግና ለመባል በማሰብ ያደረኩት እንጂ  ምንም ዓይነት መደለያ ተቀብዬ በሀገሬ ላይ ጉዳት ለማድረስ አይደለም ብለዋል፡፡

የሴጌቭ የፍርድ ውሳኔ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር የካቲት 11 ቀን የአቃቤ ህግ ቢሮ በመግለጫው ይፋ አድርጓል፡፡

ተከሳሹ ለኢራን የደህንነት ሰዎች የእስራኤልን የስለላ ሰራተኞች ስም ዝርዝር ጨምሮ በርካታ ሚስጥራዊ  መረጃዎችን  ያቀብሉ   እንደነበር በምርመራው  ፖሊስ  አረጋግጧል ነው የተባለው፡፡

ሴጌቭ  ለዚሁ የስለላ ስራቸው ሲሉ ናይጀሪያ በሚገኘው የኢራን ኢምባሲ ከቴህራን የደህንነት ሀላፊዎች ጋር በድብቅ መገናኘታቸው እና በ2012 ኢራንን ሁለት ጊዜ መጎብኘታቸውም ተደርሶበታል፡፡

የእስራኤል መገናኛ ብዙሀን ለኢራናዊያን የደህንነት ተቋም እንደ ሴጌቭ ያለ የስለላ ወኪል መመልመል እንደ ትልቅ ስኬት የሚቆጠር ነው በማለት ፅፈዋል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami