SportSports

ፒ.ኤስ.ጂ ከፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ ተሰናበተ

ፒ.ኤስ.ጂ ከፈረንሳይ ሊግ ዋንጫ ተሰናበተ

ፒ.ኤስ.ጂ ባለፉት አምስት አመታት የፈረንሳይ ሊግ ዋንጫን ማንሳት ችሏል፤ ከዚህ ውድድር የማይነቃነቅ የሚመስለው የፓሪሱ ቡድን በሜዳው ፓርክ ደ ፕሪንስ 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡

በዘንድሮው የውድድር ዓመት እስካሁን በሊግ አንድ ሽንፈት አስተናግዶ የማያውቀው ፒ.ኤስ.ጂ መራራ ሽንፈት የተጎነጨው ደግሞ በሊጉ ወራጅ ቀጠና ውስጥ በሚገኘው ገንጎ ነው፡፡

ገንጎን ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያሻገሩ ጎሎችን የፈረንሳዊው የቀድሞ ተጫዋች ሊሊያን ቱራም ልጅ መርከስ ቱራም እና የኒ ንጋባኮቶ የፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል፡፡

ኔይማር የቡድኑን ከባዶ መሸነፍ ያዳነች ግብ ከመረብ አገናኝቷል፡፡

በሌላ ጨዋታ የቴሪ ሄንሪው ሞናኮ ከሬን ጋር ተጫውቶ ሙሉ ጨዋታውን በአንድ አቻ ውጤት ቢያጠናቅቅም፤ በተሰጠው የመለያ ፍፁም ቅጣት ምት 8 ለ 7 ረትቷል፡፡

በሊግ አንድ ውድድር 19ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሞናኮ አሁንም ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት እየተፍጨረጨረ ነው፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami