በአለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በሙሉ ወደአዲስ አበባ ተጠሩ
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሁሉም የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጥሪ ማድረጉን አስታወቀ።
ከሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት እንደተገኘው መረጃ ለአምባሳደሮቹ ጥሪ የተደረገው በተለያዩ ወቅታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ለማድረግ ተብሎ ነው።
አምባሳደሮቹ ወደአዲስ አበባ የሚመጡት በቀጣዩ ሳምንት ነው ተብሏል።