ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ 147 ጠበቆች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ወሰደ
በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የጠበቆች አስተዳደር እና የነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ደምሴ እንደገለጹት በ2011ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ 147 ጠበቆች የስነስርዓት እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
እንደ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ገለፃ የተቀጡት ጠበቆች በስነ ምግባር ችግር ፣ፈቃድ በወቅቱ ባለማሳደስ እና በስነ ምግባር ችግር ጥፋተኛ የተባሉ ናቸው።