ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመች
የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረመው ገልፍ የኤሌክትሪክ ትስስር ከተባለ የባህረ ሰላጤው አባል ሀገራት የኃይል አቀርቦት ተቋም እና የዓለም አቀፉ የኃይል ትስስር ድርጅት ጋር ነው፡፡
ሰነዱ የሃይል አቅርቦትን መሰረት ያደረገ ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይም የውሃ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የባህረ ሰላጤው የኤሌክትሪክ ትስስር ባለስልጣን ስራ አስፈፃሚ አህመድ አል ኢብራሂምና የዓለም አቀፉ የኃይል ትስስር ድርጅት ሊቀመንበር ሊዮ ዚኒያ ተገኝተዋል፡፡
በአትዮጵያና በባህረ ሰላጤው ሀገራት መካከል ወደፊት በሚኖረው የሃይል ትስስር የአዋጭነት ጥናት የሰነዱ አካል እንደሆነ ከውሃ፣መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡