የእስራኤል አቃቤ ህግ ከምርጫ በፊት ኔታንያሁ ላይ ክስ ልመሰርት እችላለሁ አለ
አቃቤ ህግ የሰጠው ፍንጭ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሚያዚያ 9 ከሚካሄደው ምርጫ በፊት ሊከሰሱ እንደሚችሉ ያመላክታል ተብሏል፡፡
አቃቤ ህግ በመግለጫው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ምርጫው ከመካሄዱ በፊት እንዳይከሰሱ የሚያደርግ ህጋዊ ምክንያት የለም ነው ያለው፡፡
አቃቤ ህግ ይህን ያለው የኔታኒያሁ ጠበቃ ከምርጫው በፊት እንደዚህ ዓይነት አደናቃፊ ውሳኔ አይተላለፍም ማለታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አቪቻይ ማንዴልብሊት ከስ የመመስረት ሂደቱን ለማፋጠን ማስረጃዎችን በተቻለ ፍጥነት በመመርመር ላይ ነን ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶስት የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ክስ እንደሚጠብቃቸው የፖሊስ ምርመራ ያሳያል፡፡
እሳቸው ግን አቃቤ ህግ ፍላጎቱን ይፋ ቢያደርግም እኔን ከምርጫ ውድድር የሚያግደኝ ነገር የለም በማለት ተናግረዋል፡፡