የግብፅ ፓርላማ የአልሲሲን ስልጣን ለማራዘም ህገ መንግስት ሊያሻሽል ነው፡፡
የግብፅ ሀገ መንግስት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ከሁለት ተከታታይ ዓመታት በላይ በስልጣን እንዳይቆይ ይደነግጋል፡፡
አሁን ግን የግብፅ ምክር ቤት የፕሬዝዳንቱን ስልጣን ለማራዘም የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ቀርቦለት ከተወያየ በኋላ ከአንድ አምስተኛ በላይ በሆነ ድምፅ አፅድቆተራል፡፡
ሽንዋ እንደዘገበው ይህ አዋጅ በስራ ላይ ከዋለ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ በፈረንጆቹ 2022 የስልጣን ዘመናቸው ሲጠናቀቅ ለሶስተኛ ጊዜ መወዳደር ይችላሉ፡፡
ለፓርላማ የቀረበው ረቂቅ ህግ ፕሬዝዳንቱ ለሶስተኛ ጊዜ እንዲወዳደሩ ብቻ ሳይሆን በአንድ የምርጫ ዘመን በስራ ላይ የሚቆዩበት ጊዜ ከአራት ዓመት ወደ ስድስት ዓመት ከፍ እንዲልም ይጠይቃል፡፡
ምክንያቱ ደግሞ በሁለት የምርጫ ዘመናት ለስምንት ዓመት በቢሮ የሚቆይ ፕሬዝዳንት የግብፅን ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች ለመፍታት በቂ ጊዜ አይኖረውም የሚል ነው፡፡
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ከዚህ በተጨማሪም የመከላከያ ክፍሉን ለማጠናከር የሚያስችሉ ጉዳዮችን አካትቶ ያየዘ ነው ተብሏል፡፡
መንገሻ ዓለሙ