በኢትዮጵያ እና በብሪታኒያ መካከል ያለው ግኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የብሪታኒያ የፓርላማ ልኡካን ቡድን አባላት ተናገሩ
የልኡካን ቡድኑ አባላት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተሰፋዬ ዳባ ጋር ተወያይተዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደገለፀው በውይይቱ ወቅት የብሪታኒያ የፓርላማ ልኡክ አባላቱ ጉብኝት አላማ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር እና በፓርላማዎቹ መካከል የሀሳብ ልውውጥ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግዋል፡፡
የልኡካን ቡድኑ የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አድንቀዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው አቶ ተስፋዬ ዳባ በበኩላቸው የኢትዮጵያ እና ብሪታኒያ ግንኙኘት እ.ኤ.አ ከ1897 አም ጀምሮ የተመሰረተ መሆኑን አውስተው በባህል፣ በምጣኔ ሀብትና በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር እየሰሩ እኝደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አጠናክሮ ለማስቀጠል እና የፓርላማ አባለቱን አቅም ለማሳደግ ብሪታኒያ በአቅም ግንባታ በኩል ድጋፍ እንድታደርግ ሰብሳቢው አቶ ተስፋዬ ጠይቀዋል፡፡