የኪነጥበብ ባለሙያዎች በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ላይ ውይይት አደረጉ ፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ዙሪያ ከኪነጥበባለሙያዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት በትምህርትና ስልጠና ሙያንና ልዩ ተሰጥኦና ተክህኖ ያላቸውን ወጣቶች አቀናጅቶ ለማስተማር የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሙያዊ ምክረ ሀሳብ ወሳኝ ነው ብለዋል ፡፡
በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ዙሪያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ጨምሮ እስካሁን ወደ 700 ሺህ የሚጠጉ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በተደረገ ውይይት በርካታ ምክረ-ሀሳቦችን፣ አስተያየቶችና ጠቃሚ ግብዓቶች መገኘታቸውንም ዶክተር ጥላዬ ተናግረዋል፡፡
በፍኖተ ካርታው ዝግጅት እስካሁን በተደረገጉ የውይይት መድረኮች የማሻሻያ ሀሳቦች ተወስደው አንድ ዙር ማሻሻያ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የከኒነጥበብ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚሁ የውይይት መድረኩ ደራስያን ፣ ገጣሚያን ፣ሙዚቀኞች ፣ ቀራጽያን ፣ ሰዓሊያንና ሌሎችም የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳታፊ ነበሩ፡፡