Uncategorized

ኦሮሞ እና ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላቸው ጥቅም  በታሪክ እና በህገ-መንግስቱ መሰረት የሚፈታ ነው ተባለ

ኦሮሞ እና ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላቸው ጥቅም  በታሪክ እና በህገመንግስቱ መሰረት ቨምክክር የሚፈታ ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ

በለገጣፎ ለገዳዲ የፈረሱት ቤቶችን በተመለከተም “ህገወጥነት ሲስፋፋ እያየ ዝም ያለ አመራር እያለ ቤቶቹን ማፍረስ  ጥፋት ነው” ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት በአዳማ ከተማ ዛሬ በተጠናቀቀው 9ኛው የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤ ላይ የጨፌው አባላት  በክልሉ ሰላም፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር፣ ህገ-ወጥነትን መከላከል፣ ክልሉ በአዲስ አበባ ላይ ስላለው ጥቅም እና ተያያዠ ጉዳዮች ላይ  ላነሱት  ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።

ርዕሰ መስተዳድሩ በምላሻቸው ኦሮሞ እና ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላቸው ጥቅም  በታሪክ እና በህገ-መንግስቱ መሰረት በምክክርና ህግን በተከተለ ሁኔታ  የሚፈታ ይሆናል ብለዋል።

ለውጡን ለመቀልበስ በዳር አገር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች አሁን በአዲስ አበባ ጉዳይ አንዱን በሌላው በማስነሳት እርስ በእርስ ለማበላላት የሚፈፅሙት ተግባር ስለሆነ ህዝቡ ጉዳዩን  በጥንቃቄ ማየት አለበት ነው ያሉት አቶ ለማ።

የተለያዩ የአገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮችን ሌላ መልክ በመስጠት አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳና እርስ በእርሱ እንዲጋጭ ለማድረግ እየተፈፀሙ ያሉ ሴራዎችን መላው ህዝብ እንዲታገል ጠይቀው  ህዝቡ ጠረፍ አካባቢ ይፈፀም የነበረውን የፖለቲካ ሴራ ወደመሃል አገር ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ሴራ ሊገታ ይገባል ብለዋል።

አቶ ለማ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ በፈረሱ ቤቶች ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያም ህገ-ወጥ ቤቶች ሲገነቡ ቁጭ ብሎ የሚመለከት አመራር እያለ ቤት እንዲፈርስ መደረጉ በራሱ ጥፋት ነው ነው ብለዋል፡፡

ለልማት ፕሮጀክቶች መጓተት ዋነኛው ምክንያት የፋይናንሰ ችግር እና የተቋራጮች አቅም ማነስ እንደሆነም በጉባዔው ተነስቷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የክልሉ መንግስት በሰላም ማስከበርና በተፈናቃዮች ጉዳይ ላይ መጠመዱ የልማት ፕሮጀክቶቹ ቁጥጥር እንዲሳሳ ምክንያት መሆኑ በስብሰባው ላይ ተነግሯል፡፡

በሰላም ማስፈን ተግባር ላይ የክልሉ መንግስት ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ሰላም ለማውረድ በትእግስት ያከናወነው ተግባር በርዕሰመስተዳድሩ እንደ ስኬት ተነስቷል፡፡

በተጨማሪም ጉባኤው በአስፈጻሚ አካላት የተከናወኑ ስራዎችን በመገምገም፣ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበራት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ እና ለ290 ዳኞች ሹመት በመስጠት ተጠናቋል፡፡ ከተሾሙት ዳኞች መካከልም 19ኙ ሴቶች ናቸው ተብሏል፡፡

 

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami