በአካል ላይ የሚደርስ ጉዳት መጠንን የሚለካ መተግበሪያ በኢትዮጵያ የሙከራ ስራ ሊጀምር ነው
ይህ በአደጋም ይሁን በማናቸውም ምክንያት በአካል ላይ የሚደርስ የጉዳት መጠንን የሚለካው መተግበሪያ ስሪቱ የኢትዮጵያ ሲሆን አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑም ተነግሯል፡፡
ከዚህ በፊት የአካል ጉዳተኝነት መጠን ልኬት በዘልማድ የሚከናወን በመሆኑ በአደጋ ጊዜ በሚከፈል ካሳ መጠን ላይ በፍርድ ቤቶችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች አለመግባባቶች ይፈጠሩ ነበር።
ቴክኖሎጂው በኢትዮጵያ በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ በሆኑ አደጋዎች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች የደረሰባቸው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ አስልቶ የሚያስቀምጥ መሆኑም ተገልጿል።
ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገፅ ላይ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ይኸው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተመራማሪዎች ያሰራው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአካል ጉዳተኝነት መጠን መለኪያ መተግበሪያ እና ብሄራዊ መመሪያ የሙከራ ስራ ሊጀምር ርክክብ ተካሂዷል፡፡
ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ከተሞከረ በኋላ በሀገሪቱ የህክምና ማዕከላት ወደ ስራ ይገባል ተብሏል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ‹‹ኦርቶፔዲክስና ትራማቶሎጂ›› ማህበር ጋር ወደ ፊት አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በገፁ አስፍሯል፡፡