EthiopiaSocial

የከተማ አስተዳደሩን ለከፍተኛ የሃብት ብክነት ይዳርግ የነበረው የደመወዝ አከፋፈል ስርዓት በአሻራ የታገዘ ሊደረግ ነው፡፡

የከተማ አስተዳደሩን ለከፍተኛ የሃብት ብክነት ይዳርግ የነበረው የደመወዝ አከፋፈል ስርዓት በአሻራ የታገዘ ሊደረግ ነው፡፡

ከዚህ በፊት በሌላ ሰው ስም ፣ በስራ ገበታ ሳይገኙ እና በተለያየ የደመወዝ ፔሮል ተከፋይ በመሆን የከተማ አስተዳደሩን ላልተገባ ወጪ ሲዳርግ የቆየውን የደመወዝ አከፋፈል ስርዓት ለማስቀረት አከፋፈሉን በአሻራ የታገዘ ለማድረግ ወስኗል፡፡
ይህም በደመወዝ መልክ ይባክን የነበረውን የህዝብ ሃብት ከብክነት ለማትረፍ ይረዳል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ማምሻውን የተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ገምግሟል፡፡
በዚህም በአሁኑ ወቅት የከተማ አስተዳደሩ የካፒታልና ጠቅላላ ወጪ ከ65%-70% መድረስ የነበረበት ቢሆንም እስከ አሁን ወጪ የተደረገው ከ35%-36% ብቻ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ለአብነት ያህል ፦
• ለመንገድ ዘርፍ 6 ቢሊዮን ብር የተበጀተ ቢሆንም እስከአሁን ወጪ የተደረገው ብር 2.5 ቢሊዮን ፤
• ለውሃ ዘርፍ ከተመደበው የ4.3 ቢሊዮን ብር በጀት እስከ አሁን ወጪ የተደረገው ብር 1.4 ቢሊዮን ፤
• የጤናው ዘርፍ ከተመደበለት የ2.4 ቢሊዮን ብር እስከ አሁን ወጪ ያደረገው ብር 500ሚሊዮን ብቻ መሆኑም በመድረኩ ተነስቷል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በተጨማሪም በመልካም አስተዳደር ፣ በአልግሎት አሰጣጥ ፣ ህግን የማስከበር እና የከተማው የፀጥታ ሁኔታ ከማስጠበቅ አንፃር የተሰሩ ስራዎች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami