SportSports

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት በሚካሄዱ ጨዋታዎች ይጀመራሉ፡፡

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት በሚካሄዱ ጨዋታዎች ይጀመራሉ፡፡

 

በቻምፒዮንስ ሊጉ ወደ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ለመሸጋገር የደርሶ መልስ ግጥሚያዎች ዛሬ ምሽት በሁለት ጨዋታዎች አማካኝነት ይጀመራሉ፡፡

የእንግሊዙ ቶተንሃም ወደ ጀርመን አቅንቶ በሴግናል ኤዱና ፓርክ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ ጋር የሚፋለም ይሆናል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በነበራቸው የመጀመሪያ ግጥሚያ ዊምብሌይ ላይ ስፐርሶች 3 ለ 0 አሸንፈው የማለፍ ዕድላቸውን ሰፋ ቢያደርጉም ዶርትሙንዶች ውጤቱን ቀልብሰው ወደ ተከታ ዙር ማለፍ እንደሚችሉ እየተናገሩ ነው፡፡

ጉዳት እያለባቸው ወደ ጀርመን የተጓዙት አማካዮቹ ሃሪ ዊንክስ እና ኢሪክ ዳየር የመሰለፋቸው ነገር እርግጠኛ ያልሆነ ሲሆን ኬራን ትሪፒዬር ጭራሽ ከቡድኑ ጋር አልተጓዘም፡፡ ደል አሊ ሌላኛው ለቡድኑ ግልጋሎት የማይሰጠው ተጫዋች ነው፡፡

ሌላኛው በተመሳሳይ ሰዓት የሚደረገው የመልስ ጨዋታ ደግሞ ስፔን ላይ ሲካሄድ ሪያል ማድሪድ ሳንቲያጎ ቤርናቤው ላይ የኔዘርላንዱን አያክሳም ስተርዳምን ያስተናግዳል፡፡

ከሳምንታት በፊት አምስተርዳም ላይ ቡድኖቹ ተጫውተው ሎስ ብላንኮስ 2 ለ 1 ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

አምበሉ ሰርጂዮ ራሞስ በመጀመሪያው ግጥሚያ የመልሱ ጨዋታ ሆንብሎ እንዲያልፈው ቢጫ ካርድ መመልከቱን ያረጋገጠው የአውሮፓ እግር ኳስ ማሕበር በተጫዋቹ ላይ የሁለት ጨዋታ ቅጣት በማስተላለፉ በምሽቱ የማይኖር ይሆናል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami