EthiopiaPolitics

የዳግማዊ  አፄ ቴዎድሮስ  ሹሩባ  ወደ ሀገሩ ሊመለስ ነው ተባለ

የዳግማዊ  አፄ ቴዎድሮስ  ሹሩባ  ወደ ሀገሩ ሊመለስ ነው ተባለ

የዳግማዊ  አፄ ቴዎድሮስ  ፀጉር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ መወሰኑ ተገለፃôል፡፡

በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ  ኤምባሲ የንጉሰ  ነገስት አፄ ቴዎድሮስ  ፀጉርን  ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ የቀረበውን ጥያቄ  የለንደኑ ሙዚየም ተቀብሎታል ተብሏል፡፡

በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ  ኤምባሲ የዳግማዊ  አፄ ቴዎድሮስ ሹሩባ  ፀጉር ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በተደጋጋሚ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ፀጉሩ ለህዝብ እየታ ቀርቦ ከነበረበት ሙዚየም እንዲነሳ መድረጉ ተነግሯል፡፡

በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ  ኤምባሲ  ትላንት  ይፋ ባወጣው ጋዜጣዊ  መግለጫ የንጉሱን  ሹሩባ ወደ ሀገሩ እንደሚመለስ  አስታውቋል::

የንጉሱ ፀጉር መቼ እንደሚመለስ እና መሰል ጉዳዮችን ለመነጋገር  የፊታችን  ሀሙስ ቀጠሮ መያዙንም  ገልፃôል፡፡

ኤምባሲው በመግለጫውም  የዳግማዊ  አፄ ቴዎድሮስ  ፀጉር ወደ ኢትዮጵያ  መመለሱ  በሁለቱ ሀገሮች መካከል እያደገ የመጣው ሁለንተናዊ ግንኙነት ማሳያ ነው ብሏል፡፡

በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ  ኤምባሲ በበኩሉ  የዳግማዊ  አፄ ቴዎድሮስ ፀጉር  ለተቀመጠበት  ሙዚየም ምስጋና አቅርቧል፡፡

ዳግማዌ አጼ ቴዎድሮስ በእንግሊዙ  የጦር መሪ  ፊልድ ማርሻል ለሚመራው ጦር አልማረከም በማለት  መቅደላ  ላይ እራሳቸውን  ማጥፋታቸው ይታወሳል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami