SportSports

ቁልፍ የብሔራዊ ቡድን ተጠሪዎች ለሀገራቸው ግልጋሎት አይሰጡም

ከነገ ጀምሮ የብሔራዊ እግር ኳስ ቡድኖች የወዳጅነት እና የማጣሪያ ግጥሚያዎች በተለያዩ ዓለማት ይከናወናሉ፡፡

ለነዚህ የብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታዎች ተጫዋቾች ከክለቦቻቸው ተነጥለው ወደ ሀገሮቻቸው ስብስብ አምርተዋል፡፡

ከሩሲያው ዓለም ዋንጫ በኋላ ለአርጀንቲና ግልጋሎት ያልሰጠው ሊዮኔል ሜሲ በስፔን መዲና ማድሪድ ላይ ዝግጅቱን እያደረገ ያለውን የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተቀላቅሏል፡፡ ቡድኑ ቬንዙዌላ እና ሞሮኮ ላይ ወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

…………………………….

ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል በጉዳት እና በሌሎች ምክንያቶች የማይሰለፉት እየተበራከቱ ነው፡፡

የሊቨርፑሉ ሲውዘርላንዳዊ አማካይ ዤርዳን ሻኪሪ በብሽሽት ጉዳት ምክንያት ሀገሩ ወደ ጆርጂያ አቅንታ እና ሜዳዋ ላይ ከዴንማርክ ጋር ለሚኖራት ጨዋታ ተሰላፊ አይሆንም ተብሏል፡፡

………………………………

ኮለምቢያዊው ዳቪድ ኦስፒና በጣሊያን ሴሪ ኤ ክለቡ ናፖሊ ከዩድንዜ ጋር ባደረገው ጨዋታ በገጠመው ጉዳት ለረዥም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል ተብሎ ቢሰጋም፤ በፍጥነት ከህመሙ አገግሞ ለጨዋታ ዝግጁ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ የህክምና ባለሙያዎቹ ግን ተጫዋቹ ምንም ስጋት ባይኖርበትም ጥቂት እረፍት እንደሚያስፈልገው የተናገሩ በመሆኑ፤ ለሀገሩ ግልጋሎት ሊሰጥ እንደማይችል እየተነገረ ይገኛል፡፡

……………………………

ሌላኛው የሊቨርፑል ስኮትላንዳዊ የግራ ተመላላሽ ተጫዋች አንዲ ሮበርትሰን የስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት እያገለገለ ቢሆንም ቡድኑ ከካዛኪስታን ላለበት ጨዋታ እንደመይሰለፍ ተረጋግጧል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ተጫዋቹ የአፍ ቀዶ ጥገና የሚያደርግ በመሆኑ ነው፡፡

……………………………….

የማንችስተር ዩናይትዱ ቤልጂየማዊ አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ ለብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ዝግጅት ወቅት፤ ልምምድ ቦታ ላይ ጉዳት አስተናግዶ፤ በዚህ ሳምንት ከሚደረጉ ሁለት የብሔራዊ ቡድኑ የዩሮ 2020 የማጣሪያ ጨዋታዎች ውጭ ሁኗል፡፡

የሉካኩ ጉዳት ከጨዋታ እንደሚያግደው የታወቀው እግሩ ላይ የኤም.አር. አይ ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ነው፡፡

…………………………………..

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami