AccidentEthiopia

የቦይንግ 737 አውሮፕላን የመረጃ ሳጥን ትንተና በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የቦይንግ 737 አውሮፕላን የመረጃ ሳጥን ትንተና በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ነው ይህን ያለው፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ኢት 302 በደረሰው አደጋ መረጃ ሳጥኑ ላይ የተገኙ መረጃዎች በአዲስ አበባ በመነበብ ላይ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የአውሮፕላን አደጋ መከላከልና ምርመራ ቢሮ የሚመራ ቡድንን ጨምሮ የአሜሪካው ብሔራዊ የትራንሰፖርት ደህንነት ቢሮ፤  የፈረንሳይ   የአደጋ ምርመራ ቢሮ እና የአውሮፓ ህብረት የአቪሽን ደህንነት ኢጀንሲ  በጋራ በመሆን  የመረጃ ሳጥኑ  የኮከፒት መቅረፀ ድምፅ እና የበረራ ዳታ መቅረፀ ድምፅ ላይ የተገኘውን መረጃ በመተንተን ላይ እንደሚገኙ መኒስቴሩ ተገልጿል፡፡

የትንተናው የመጀመሪያ ውጤትም በአለም አቀፍ የሲቪል አቭዬሽን ሪፖርት የሚገለፅ ይሆናል ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በድረ ገፁ ይፋ አድርጓል፡፡

 

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami