EthiopiaSportSports

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ቡድን በማሊ አቻው ተሸነፈ

በ2020 ለሚካሄደው የቶክዩ ኦሊምፒክ ውድድር ተሳትፎ ለማግኘት የማጣሪያ ውድድሩን እያደረገ የነበረው የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች የወንዶች ብሔራዊ ኦሊምፒክ ቡድን በሁለተኛው ዙር የመልስ ጨዋታ በማሊ አቻው ትናንት ባማኮ ሞዲቦ ኬይታ ስታዲየም ላይ የ4 ለ 0 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡

ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ላይ የተካሄደውን የመጀመሪያ ሁለቱ ቡድኖች በአንድ አቻ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል፤ የማሊ ብሔራዊ ቡድን በድምር ውጤት 5 ለ 1 አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር መሻገሩን ሲያረጋግጥ፤ ኢትዮጵያ ከውድድሩ ማጣርያ ተሰናብታለች፡፡

የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች የወንዶች ብሔራዊ ኦሊምፒክ ቡድን በማሊ 5-1 ድምር ውጤት ተሸንፎ ተሰናብቷል::

ለማሊ የማሸነፊያ ጎሎችን ዲያዴ ዲያንካ በፍፁም ቅጣት ምት እና በጨዋታ ሁለት እንዲሁም አሌይ ማሌ እና አብዱላይ ዲያቤ ማስቆጠር ችለዋል፡፡

በቀጣይ ማሊ ከሌላኛዋ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር የምትጫወት ሲሆን የምታሸንፍ ከሆነ ከ23 ዓመት በታች ለሚካሄደው ውድድር የምታቀና ይሆናል፡፡

በሶስተኛው ዙር አሸናፊ የሚሆነው ብሔራዊ ቡድን በግብፅ አስተናጋጅነት ለሚሰናዳው ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተካፋይ ይሆናል፡፡

ከ23 ዓመት በታች ውድድሩ ከ1 እስከ ሶስት የሚወጡ ሀገራት ለቶኪዮ ኦሊምፒክ አፍሪካን ወክሎ የሚካፈል ይሆናል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami