በርካታ ኮንጓዊያን ኢቦላ አለ ብለው እንደማያምኑ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡
በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ በተደረገ ጥናት ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው ሰዎች መካከል ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉት ነዋሪዎች ኢቦላ በትክክል አለ ብለው አያምኑም፡፡
ህዝቡ ይህን እውነታ መቀበል አለመቻሉ በስራቸው ላይ ትልቅ እንቅፋት እየተፈጠረባቸው መሆኑን የጤና ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው አስካሁን በዲሞክራክ ሪፓብሊክ ኮንጎ 639 የሚሆኑ ሰዎች በኢቦላ በሽታ ህይዎታቸው ቢያልፍም ኮንጓዊያን ግን ለነገሩ ቁብ የሰጡት አይመስሉም፡፡
በጥናቱ ከተካተቱት 961 ሰዎች መካከል 25 በመቶ የሚሆኑት ኢቦላ የሚባል ህመም የለም የሚሉ ሲሆኑ 45.9 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በሽታው መኖሩን ባይክዱም አሁን ተከስቷል የሚሉት ግን የኮንጎን መረጋጋት የማይፈልጉ ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡
በምስራቃዊ ኮንጎ ስራ ላይ የተሰማራው የዓለም አቀፉ የነብስ አድን ኮሚቴ አባል ጣሪቅ ሪብል የጥናቱ ውጤት እኛ በስራ ላይ የሚያጋጥመንን እውነታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው ብሏል፡፡
እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2013 እስከ 2016 ባለው ጊዜ በምእራብ አፍሪካ ሀገራት የተከሰተው የኢቦላ ቫይረስ ከ11 ሺህ 300 በላይ ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት ባወጣው ሪፖርት በዲሞክራክ ኮንጎ በየሳምንቱ በአማካይ ቢያንስ ከስምንት ያላነሱ ሰዎች በኢቦላ ህመም እንደሚጠቁ ይፋ አድርጓል፡፡
መንገሻ ዓለሙ