የአርመኒያ መንግስት ለኢትዮጵያ 51 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኢኖቬሽን ማበልፀጊያ ማዕከላት ግንባታ ላይ ሙሉ ድጋፍ ሊያደርግ ነው፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኃላፊዎች በአርመኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተመራ ልኡክ ጋር ሀገራቱ በኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ዘርፍ በጋራ በሚሰሩባቸው መስኮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
የአርመኒያ መንግስት በኢትዮጵያ በተመረጡ 51 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኢኖቬሽን ማበልፀጊያ ማዕከላት ግንባታ ለማድረግ ላይ ሙሉ ድጋፍ ማድረጉ ተግለጿል፡፡
የአርሚኒያ መንግስት አርማዝ የተሰኘ የኢኖቬሽን ማበልፀጊያ በሀገሪቱ ባሉ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ ውጤት በማምጣቱ ነው በኢትዮጵያም እንዲዘረጋ እንቅስቃሴ የተጀመረው፡፡
አርመኒያ በኤሌክትሮኒክስ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ፤ በክፍተኛ ቴክኖሎጂ የስራ እድል ፈጠራ፤ በኢንተርኔት አገልግሎት በጥቅሉ በአይ ሲ ቲ ዘርፍ ጥሩ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገራ ናት፡፡
ይህንን ልምዷን ለኢትዮጵያ ለማካፈል ፍላጎት እንዳላት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዞሃርብ ናሳካኒያን በኩል ይፋ እድርጋለች፡፡
ኢትዮጵያ እና አርመኒያ በጋራ የምርምር ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የአውሮፓ ህብረትን ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸትም የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው የኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል፡፡
ቀበሌ እና ወረዳ ላይ የሚሰጥ የመንግስት አገልግሎትን ለማቀላጠፍ የአረመኒያ ተሞክሮ ጠቀሜታው የጎላ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና የአርመኒያ ኢንተርፕራይዝ ኢንኩቤሽን ፋውንዴሽን በጋራ ለመስራት የሚስችላቸውን ስምምነትም ተፈራርመዋል፡፡