EconomyEthiopia

ኢትዮጵያ ቡናን እሴት ጨምራ በመላክ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ 80 በመቶ ለማሳደግ እየሰራሁ ነዉ አለች፡፡ 

ኢትዮጵያ ቡናን እሴት ጨምራ በመላክ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ 80 በመቶ ለማሳደግ እየሰራሁ ነዉ አለች፡፡
ቴክኖሎጂን በመጠቀምና ቡናን እሴት ጨምሮ ወደ ውጭ በመላክ ኢትያዮጵያ ሀገራዊ የቡና ምርት ግብይት ላይ እሴት ለመጨመር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ምክክር መድረክ በጅማ ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሄዷል።
የምክክር መድረኩ በጅማ ከተማ የተገነባውን የኢንዱስትሪ ፓርክ በመጠቀም በአካባቢው የሚገኘው ቡና ላይ እሴት በመጨመር ለአለም ገበያ ማቅረብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ  ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ለዘመናት ሌሎች ሀገሮች የሀገራችንን ቡና እሴት በመጨመር ሲያገኙት የነበረውን ገቢ ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስቀረት ይሰራል ብለዋል።
ቡናን በጆንያ ወደ ውጭ ከመላክ የዘለለ ስራ አልተሰራም ያሉት ሚኒስትሩ፤ የቡና ምርት ላይ እሴት በመጨመርና በኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት ውስጥ በማስገባት ኢትዮጵያ የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ የሚያስችል ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን  ተናግረዋል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami