EthiopiaHealth

የስልጤ ዞን ምራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ነዋሪዎች ነፍሰጡር እናቶችን እየተንከባከቡ ነዉ፡፡

የስልጤ ዞን ምራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ነዋሪዎች ነፍሰጡር እናቶችን እየተንከባከቡ ነዉ፡፡

በስልጤ ዞን ምራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ነብሰጡር እናቶች ለመውለድ ቀናቸው ሲቃረብ ቤታቸው  ለጤና ጣቢያው የሚርቅ እናቶች እንዳይንገላቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ማረፊያ አዘጋጅተው እስከሚወልዱበት ቀን ድረስ እንክብካቤ ሳይቋረጥባቸው እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡

ከእርጉዝ እናቶች ማቆያ አገልግሎት ባሻገር በአካባቢው የሚገኙ ባለባጃጆችም  በወረዳው የሚገኙ ባጃጆችን በመደራጀት ለእርጉዝ እናቶች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡

ማህበረሰቡ ይህን ማቆያ አዘጋጅቶ ለእናቶች እንክብካቤ ሲያደርግ ከእለት ጉርሱ ቀንሶ እንጂ የትኛውም የመንግስት አካል ድጋፍ አላደረገለትም፡፡

ሰሞኑን የጤና ሚኒስቴር አመራሮች እና የሚዲያ አካላት በዚሁ ወረዳ ተገኝተው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በሌሬ ጤና ጣቢያ እናቶች ከመውለጃ ቀናቸው ቀደም ብለው የሚያርፉበት የእናቶች ማቆያ እና የአካባቢው ባለባጃጆች ትኩረትን ስበዋል፡፡

በሊሬ ጤና ጣቢያ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባው የእናቶች ማቆያ ከሩቅም ከቅርብም አካባቢ የሚመጡ እናቶች ከመውለጃ ጊዜያቸው ቀደም ብለው መጥተው የሚያርፉበት ሲሆን እስከ መውለጃ ጊዜያቸውም በቤታቸው የሚያገኙት ማናቸውም ነገሮች ሳይጓደሉ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ በተለይ ለህክምና ጣቢያዎች የሚርቅ መኖሪያ ቤት ያላቸው እናቶች ጤና ጣቢያ እስከሚደርሱ በወሊድ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች እንዳያጋጥማቸው እና የእናቶችን ሞት ከመቀነስ አንፃር  የነዋሪዎቹ  ስራዎች  የሚያስደንቅ  ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በተለይም እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ በባለሙያዎች የሚደረገው ክትትል ፤ ከወለዱ በኋላም ወደ ቤት መልሶ የሚያደርሳቸው የባጃጅ አገልገሎት በፈቃደኝነት በተደራጁ ወጣቶች በነጻ መሰጠቱ ለሌሎች ወረዳዎች አርአያ እንደሆነም ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ በራሱ ተነሳሽነት አምቡላንስ በመግዛትና የእናቶች ማቆያ ቤቶችን በመገንባት ትልቅ ስራም ሰርቷል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami