ጫማ የሰሞኑ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ዘዴ ሆንዋል አለ ገቢዎች ሚኒስቴር
በጫማ ስር ተደብቆ ሲጓጓዝ የነበረ ከ779 ሺህ ብር በላይ የሆነ የአሜሪካን ዶላር በቁጥጥር ሥር ዉሏል፡፡
ግለሰቡ ሀያሶስት ሺ ሃምሳ ዶላር በጫማ ውስጥ አድርጎ ለማሳለፍ ሲሞክር በጉምሩክ ፈታሾች ተይዟል፡፡
ሌላም ግለሰብ በተመሳሳይ /አራት ሺ አንድ መቶ/የአሜሪካን ዶላር በህገወጥ መንገድ ሊያስወጣ ሲል በቶጎጫሌ ኬላ ላይ ተይዟል፡፡
ባለፈዉ ሳምንት የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች በተጫማቸው ጫማዎች በእግር መረገጫ ስር ተረግጠው ከሀገር ሊወጡ ሲሉ መያዛቸዉ ይታወሳል