AfricaPolitics

ሊቢያዊያን ወደ ጎረቤት ቱኒዚያ ስደት ጀምረዋል፡፡

ሊቢያዊያን ወደ ጎረቤት ቱኒዚያ ስደት ጀምረዋል፡፡

በጄኔራል ሀፍታር ታማኝ ወታደሮች እና ዓለም አቀፍ እውቅና ባለው ትሪፖሊን መንግስት ጦር ሰራዊት መካከል ውጊያ ስጋት የገባቸው የሀገሪቱ ዜጎች ህይዎታቸውን ለማዳን ስደትን መርጠዋል፡፡

አሁን ላይ ወደፊት እየገሰገሰ ያለው የሀፍታር ጦር ትሪፖሊን ሳይቆጣጠር እንደማይመለስ ምሎ እየተገዘተ ይገኛል፡፡

በአንፃሩ  የፋይዝ አልሳራጅ መንግስት የተቃዋሚ ሀይሎችን አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ወደ መጡበት እንደሚመልሳቸው ቃል ገብቷል፡፡

የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ነገሩኝ ብሎ አልጀዚራ እንደዘገበው በሁለቱ ሀይሎች ግብግብ ሳቢያ ህይዎታቸው አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የሰጉ ከ500 በላይ ዜጎች ድንበር ሊያቋርጡ ሲሉ ተይዘዋል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami