EthiopiaHealth

1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በአይነቱ ልዩ የሆነ የህፃናት ሆስፒታል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው

1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በአይነቱ ልዩ የሆነ የህፃናት ሆስፒታል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው

የኢትዮጵያ መንግስት ከኔዘርላንድ መንግስት ጋር በመተባበር በ877 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ በአለርቲ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ በአይነቱ ልዩ እና የመጀመሪያ የሆነ አዲስ የህፃናት አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት በህፃናት ዙሪያ የሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶችን ማሻሻልና ማዘመን አስፈላጊ ከመሆኑ አንጻር ሆስፒታሉ በህፃናት ዙሪያ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ የልብ፣ነርቭ፣የኩላሊት እንዲሁም ከ30 በላይ የሚደርሱ የህክምና ስፔሻሊቲ አገልግሎት እንደሚኖሩት ተናግረዋል፡፡

በአለርት ሆስፒታል ውስጥ የሚገነባው የህፃናት አጠቃላይ ሆስፒታል በሁለት አመት እንደሚጠናቀቅና 317 አልጋዎች እንደሚኖሩት ወጪውም በኔዘርላንድ መንግስት፣በአሜርካን ፋውንደሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት እንደሚሸፍን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami