EconomyEthiopia

የገቢዎች ሚኒስቴር 1 ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡ ተነገረ

የገቢዎች ሚኒስቴር 1 ነጥብ 07 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡ ተነገረ
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አበቤና ሌሎች የስራሃላፊዎች የጉምሩክን በሚመለከት ወደ 2.5 ቢሊየን ብር በጉድለት የተገኘ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ 1.07 ቢሊየን መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ አዳነች የሃገር ውስጥ ታክስን በሚመለከት 11 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ያሉ ሲሆን 8.1 ቢሊየን ብር ሊሰበሰብ እንደሚገባ በኦዲት የቀረበ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1.1 ቢሊየን ተሰብስቦ ቀሪው በሂደት ላይ መሆኑንም  ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ተናግረዋል፡፡

ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተሟላ ባይሆንም እያደረጉ ያለው የማስተካከያ እርምጃ ጥሩ መሆኑን አንስተው ይሰብሰብ ከተባለው ግብር ውስጥ ያልተሰበሰቡ መኖራቸው፣ ከበጀት አጠቃቀም ጋር በርካታ ግኝቶች መኖራቸው፣ ያለአግባብ የተከፈለ የትርፍ ሰአት ክፍያ፣ ከተሰብሳቢ ጋር ተያይዞ በወቅቱ ያልተወራረደና ከማን እንደሚሰበሰብ ግልጽ ያልሆነ ሂሳብ፣ ተከፋይን በሚመለከት በወቅቱ ያልተወራረደ ሂሳብ መኖሩንና ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
መረጃው የህዝብ ተወካች ምክርቤት ነው፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami