SportSports

በዩሮፓ ሊግ አርሰናልና እና ቼልሲ ድል አድርገዋል

ትናንት ምሽት የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

በምሽቱ በጉጉት በተጠበቀው ጨዋታ አርሰናል በኤመሬትስ ስታዲየም ናፖሊን አስተናግዶ 2 ለ 0 ድል በማድረግ ለመልሱ ግጥሚያ ሸክሙን አቅልሏል፡፡

በግሩም ቅብብል አሮን ራምሴ ላይ የደረሰችው ኳስ 14ኛው ደቂቃ ላይ ወደ ግብነት ተቀይራ መድፈኞቹ ቀዳሚ መሆን ችለዋል፡፡

ከአስር ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ ከሉካስ ቶሬራ የተሻገረችውን ኳስ የናፖሊው ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ጨርፎ እራሱ መረብ ላይ አሳርፏል፡፡

በጨዋታው መድፈኞቹ የበላይነት የነበራቸው ሲሆን ከዚህ በበለጠ የግብ መጠን እንዳያሸንፉ የናፖሊው ግብ ጠባቂ አሌክስ ሜሪት ሚና ጉልህ ነበር፡፡

የመልሱ ፍልሚያ ቀጣይ ሳምንት ሳን ፓውሎ ላይ ይደረጋል፡፡

ወደ ቼክ የተጓዘው ቼልሲ የሀገሪቱን ቡድን ስላቪያ ፕራሃ በሜዳውና እና ደጋፊው ፊት 1 ለ 0 ሲረታ ፤ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ጎል ስፔናዊው ማርኮስ አሎንሶ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ አራት ደቂቃዎቸች ሲቀሩ ከመረብ አገናኝቷል፡፡

ለሰማያዊዎቹ ከባድ በነበረው ምሽት ለመልሱ የስታንፎርድ ብሪጅ ግጥሚያ መልካም አስተዋፅኦ ያለው ውጤት ይዞ ተመልሷል፡፡

በሌሎች ግጥሚያዎች ቫሌንሲያ ከሜዳው ውጭ በእስታዲዮ ዴ ላ ሴራሚካ ቪያሪያልን 3 ለ 1 ሲረታ ፤ ቤንፊካ ዳ ሉዝ ላይ አይንትራክት ፍራንክፉርትን 4 ለ 2 አሸንፏል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami