የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን የፍትህ ተቋማት ለማጎልበት የሚያስችል የ4 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ፡፡
የአሜሪካ አለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት የሚደገፍው ፍትህ የተሰኘው ይህ ፕሮጀክት ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓቱን ጠንካራና ገለልተኛ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ ለጠቅላይ አቃቤ ህግ የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ገለልተኛ ውሳኔ እንዲወስኑ አቅማቸውን የማሳድግ ስራ ይሰራል ነው የተባለው፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ጠንካራ የችሎት ስርዓት እንዲኖራቸው እና የፍርድ ሂደቱን ቀልጣፋ ማድረግ የድጋፉ አካል መሆኑንም የአሜሪካን ኤምባሲ ለአርትስ ቴሌቪዠን የላከው መግለጫ ያስረዳል፡፡
አሜሪካ ላለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ ለልማት ስራዎች እና ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል 4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ማድረጓ በመግለጫው ተመልክቷል።