ኩባዊያን ዶክተሮች ባልታወቁ ታጣቂዎች ታገቱ፡፡
በሶማሊያ አቅራቢያ ባለው የኬንያ ድንበር ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች አንድ የፖሊስ ኦፊሰር ገድለው 2 ኩባዊያን ሀኪሞችን አግተው ወስደዋል ተብሏል፡፡
ደይሊ ኔሽን እንደዘገበው የኬንያ ፖሊስ ይህን ድርጊት የፈፀሙት ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያለው የአል ሸባብ ቡድን አባላት ናቸው የሚል ጥርጣሬ አለው፡፡
አደጋውን ተከትሎ ፖሊስ ወደ ሶማሊያ ድንበር አካባቢ የሚወስደውን መንገድ ለጊዜው እግ እንዲሆን አድርጓል ነው የተባለው፡፡
አሁን አደጋው በተከሰተባት የማንዴራ ካውንቲ ከወራት በፊትም ሁለት ህፃናትን ጨምሮ አምስት ሰዎች በተመሳሳይ መልኩ በታጣቂ ሀይሎች በድንገት ታፍነው ተወስደዋል፡፡
ባለፈው ማክሰኞ የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው የደህንነት ጥቃቄ መለእክት ዜጎቹ ወደ ማንዴራ ካውንቲ ጉዞ እንዳይደርጉ አስጠንቅቆ እንደነበርም ዘገባዎች ያሳያሉ፡፡
በኬንያ የሽብር፣ የእገታ እና ሌሎች ወንጀሎች መደጋገማቸውን ተከትሎ በየጊዜው የሚሰጡ የማጠንቀቂያ መልእክቶች በመራከታቸውም ተስቷል፡፡
መንገሻ ዓለሙ