EthiopiaSocial

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የቃጠሎ ሁኔታ አሁንም በቁጥጥር ሥር አልዋለም፡፡

የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የቃጠሎ ሁኔታ አሁንም በቁጥጥር ሥር አልዋለም፡፡

የአማራ ክልል አካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በላይነህ አየለ ለአብመድ እንደተናገሩት ከትናንት ጀምሮ በሄሊኮፕተር ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

ሄሊኮፕተሯን በአካባቢው አንቀሳቅሶ እሳቱን ለማጥፋት መልክአ ምድሩ ተጽእኖ እንዳላሳደረበት ከአብራሪው ማረጋገጣቸውንም ተናግረዋል፡፡

ሄሊኮፕተሯ እስከ 1ሺህ 300 ሊትር ውኃ ከደባርቅ አካባቢ አሰራ ወንዝ በመቅዳትና በእሳቱ ላይ በመርጨት ለማጥፋት እየሠራች እንደሆነ ዶክተር በላይነህ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ሄሊኮፕተሯ አንድ ጊዜ በሞላችው ነዳጅ ለ3፡00 ብቻ ስለምትሠራ ነዳጅ ለመሙላት ወደ ጎንደር በመሄድ ጊዜና ነዳጅ ታባክናለች ነው ያሉት፡፡

የአውሮፕላን ነዳጅ የተለየና ከማንኛውም ማደያ የሚቀዳ ባለመሆኑ በቦቴ ተጭኖ ደባርቅ ድረስ እንዲቀርብልን ጠይቀን ምላሽ እየጠበቅን ነው›› ያሉት ዶክተር በላይነህ ምላሹ እስኪመጣ ወደ ጎንደር እየተመላለሰች መቅዳቷ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በፓርኩ ሁኔታውን እየተከታተሉ የሚገኙት ዶክተር በላይነህ አየለ አንድ ሄሊኮፕተር በቂ አለመሆኑን ገለጸው የእስራኤል የእሳት ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ቡድን በፍጥነት የሁኔታ ግምገማ አድርገው ተጨማሪ የእሳት ማጥፊያ አውሮፕላን እንዲሰማራ ያደርጋሉ ብለው ተስፋ እንዳደረጉ ገልጿል፡፡

ምንጭ፤- አብመድ

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami