ጉዳት የደረሰባቸዉን የአካል ክፍል የሚተኩ (የአካላዊ ተሃድሶ ህክምና በሁሉም መንግስት ጤና ተቋማት ሊሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ቀደም ሲል በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ስር የነበሩ የአካላዊ ተሃድሶ ህክምና ተቋማት ሙሉ ለሙሉ ወደ ጤና ሚኒስቴር እንዲዛወሩ በተገባው ውል መሰረት የርክክብ ስራ እየተሰራ ነዉ፡፡
የጤና ሚኒስቴር የክሊኒካል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አባስ ሀሰን በጉዳዩ ላይ በተደረገ ዉይይት ላይ እንደተናገሩት የጤና አገልግሎት እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም የአካላዊ ህክምና አገልግሎት መካተት አለበት ብለዋል፡፡
በየጤና ተቋማት የአካላዊ ተሃድሶ ህክምና ትኩረት ያልተሰጠው በመሆኑ ታካሚዎች ህክምናው ለመውሰድ ይቸገራሉ ተብሏል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ 11 የአካላዊ ተሃድሶ ህክምና እየሰጡ ያሉ ማዕከላት ሲኖሩ ህክምናዉን በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎችና ጤና ተቋማት ወጥ በሆነ መንገድ ለመስጠት አራት ምዕራፎች ያሉት መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ በአካላዊ ተሃድሶ ህክምና የአለርት ሆስፒታል ጥሩ ተሞክሮ እንዳለዉ ከጤና ሚኒስቴር ሰምተናል፡፡