EthiopiaHealth

በአርሲ ዩኒቨርሲቲ በኢንተርን ሀኪሞች ላይ የደረሰውንጉዳት እንዳሳዘነዉ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በአርሲ ዩኒቨርሲቲ በኢንተርን ሀኪሞች ላይ የደረሰውንጉዳት እንዳሳዘነዉ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በአገራችን እየተካሄደ ባለው ሁሉን አቀፍ ሪፎርም ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ ጀምሮ የተለያዩ ሰብአዊና ህጋዊ መብቶች እንዲከበሩ መንግስት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል::

የህክምና ባለሙያዎች እንደማንኛውም ግለሰብና ባለሙያ ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ የማቅረብ መብት እንዳላቸው በጽኑ ይታመናል ብሏል የጤና ሚኒስቴር ፡፡

የጤና ሚኒስትሩ በትላንትናዉ  እለት  በአርሲ ዩኒቨርስቲ ኢንተርን ሀኪሞች ጥያቄዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ለዩኒቨርስቲው አመራሮች ለማቅረብ በወጡበት ወቅት በአከባቢው የሚገኘው ስርዓት አስከባሪ የኃይል እርምጃ በመውሰድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ከደረሰን ሪፖርት መረዳት ተችሏል  ብሏል::

በደረሰው ጉዳት የጤና ሚኒስቴር እጅጉን ያዘነ ስሆን ይህንን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል::

ጉዳቱን ያደረሱ አካላትም በአስቸኳይ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ ተገቢው ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እየሰራ ይገኛል ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami