የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ከመጋቢት እስከ መጋቢት የተሠሩ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን የሚገመግም የሁለት ቀን የምሁራን አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው፡፡
አውደ ጥናቱ የአንድ ዓመቱን ሂደት በምሁራዊ ደርዝ ለመዳሰስ፣ ለመገምገምና ለመመርመር ያለመ ነው፡፡
30 ምእራፎችን በሚያካትተው የጥናት መጽሐፍ ላይ የሚወጡ የጥናትና ምርምር ሥራዎች የሚገመገሙበት የሁለት ቀን የምሁራን ውይይት ከሚያዝያ 12 ቀን 2011 ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን በኢትዮጵያ ላይ መጠነ ሰፊ ጥናት ያካሄዱ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ምሁራን ተሳትፈውበታል፡፡
ይህ የጥናት መጽሐፍ የፖለቲካ ለውጥና ተሐድሶ፣ የኢኮኖሚ ዘርፍ ለውጥ፣ ሀገረ ብሔር/ሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ የውጭ ግንኙነትና የሀገር ደኅንነት የሚሉ አራት አንኳር ርእሰ ጉዳዮችን የሚዳስስ ይሆናል ተብሏል።
ምንጭ ፤-የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት