ቱርክ ሲሰልሉኝ ደረስኩባቸው ያለቻቸውን ሁለት የዓረብ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦችን አሰረች፡፡
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ቱርክ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸው እነዚህ ግለሰቦች ለተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ሲሰልሉ እንደነበር የእምነት ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
ከሰላዮቹ አንዱ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2018 ወደ ቱርክ የገባ ሲሆን ቀኑ ደግሞ ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ በተገደለ ማግስት ነው ተብሏል፡፡
የቱርክ መንግስትም የሰላዮቹ ተልእኮ ከጋዜጠኛው ግድያ ጋር ግንኙነት ይኑረው አይኑረው ለማወቅ ምርመራውን አጠናክሮ አንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
የሳውዲ ምንግስት በጀማል ካሾጊ ግድያ እጁ አለበት በሚል ከበርካታ ሀገራት ትችት ቢደርስበትም ሪያድ ግን ማስረጃ የሌለው ስም ማጥፋት ነው በሚለው አቋሟ እንደፀናች ናት፡፡
መንገሻ ዓለሙ